Saturday, May 12, 2012

http:///? www.meleket4u.blogspot.com/

Thursday, May 10, 2012


ማን አሸነፈ?

በቤተክርስቲያን አሸናፊ አይኖርም ብሎ መረዋ የጻፈው ከ ፫ ዓመት በፊት ነበር። መረዋ ዛሬም ማንም አሸናፊ አይደለም ብሎ ያምናል። እንዴውም የገደለው ባሌ የሞተው ወንድሜ የሚለውንም እንደ ምሳሌ መጠቀሙን ያስታውሳል። እንሆኝ የቤተክርስቲያናችን ውጣ ውረድ ከተጀመረ ከ ፬ ዓመት በላይ ሆኗል።
ይህ ሁሉ ውጣ ውረድ ይህ ሁሉ ክስ የመጣው ደግሞ ከሳሾች ገንዘብ ፈልገው አልነበረም።
ቢሆንማ ኖሮ ካሳ በጠየቁ ነበር።
ለስልጣን ብለውም አልነበረም።
ቢሆንማ ኖሮ ምእመን ሳይወያዩበት በቦርዱ "ጸደቀ" የተባለው መተዳደሪያ ደንብ ለተመራጭ አስተዳዳሪዎች የፈላጭ ቆራጭ ስልጣን የሚሰጥ ነበር።
ለንብረትም አልነበረም።
ቢሆንማ ኖሮ የንብረት ክስ ከተመሰረተ ፍርድ ቤቱ ያገባዋልና ይወስንላችኋል ሲባል የንብረት ክስ አንመሰርትም ባላሉ ነበር።

ነገሩ የመብት ጉዳይ ሆነና ይኸው እስካሁን እያወዛገበ ይገኛል። ለስለሰብአዊ መብት እንከራከራለን የሚሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች መብት እንንፈግ ብለው ሲዶልቱ መክረማቸውን ያያችሁት ጉዳይ ነው ። በመብቴ አልደራደርም ያለው አባል ከአባልነት እራሱን እያሸሸ ለመምጣቱ ደግሞ ምስክር መጥራት የሚያስፈልግ አልመሰለንም። ምስክሩ እናንተ ናችሁና።

፴ ብር ለይሁዳም አልበጀምና ተው ሲባል ሰሚ አልነበረም። ይህ ግን ቤተክርስቲያኑን አደኸየ እንጂ አልጠቀመም።
አቶ ኃይሉ እጅጉ በመሰረቱት ቤተክርስቲያን አዳራሽ ለመብት ቆመሃልና አትገባም ሲባሉ የዓይን ምስክር ነበርን። ነበራችሁ።
አቶ ሙላው ወራሽ እንደ ወረደባቸው አሉባልታና የስም ማጥፋት ዘመቻ አገር ለቀው ይወጣሉ ብለው የጠበቁ ቢኖሩ የሚያስገርም አልነበረም።ያ ግን አልሆነም።

ደጋፊም ተቃዋሚም አሁንም አንድላይ ነን። አሁንም አንድ ላይ እያስቀደስን ነው ማለት እውነት ነው። ጸሎታችንን እኩል ይሰማል ማለት ግን አጠያያቂ ይሆናል። ትላንት ከአዳራሽ ያስወጡ የነበሩ እራሳቸው እንደወጡ ያያችሁት ነውና መድገም አያስፈልግም።

ሰባት ጊዜ ሽማግሌ አናግረናል የሚሉት የመብት ተከራካሪዎች፡ ሰባቱንም ጊዜ ከሽማግሌዎች ጋር በአክብሮት ተወያይተን ተለያይተናል ብለው በልበ ሙሉነት ይናገራሉ። በምስጋና የተለያዩት የመብት ተከራካሪዎች፣ የሚኮሩበት ጉዳይ ቢኖር ሽማግሌዎቹን ማሳመን መቻላቸው ብቻ ሳይሆን ከመሃከላቸው ደጋፊና አብሯቸው የሚታገል ማትረፋቸው ነው። የዛሬ ሳምንት በቤተክርስቲያን የቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት ሁለቱም ወገኖች ታረቁ ተብሎ ሲነገር ሕዝቡ እልል ሲል ያየ ቢያለቅስ ምን ይፈረድበታል? ሁኔታው ግን ሰዓታትም ሳይቆይ እርቅ ፈርሷል ተባለና ተቀየረ። ማን እንዳፈረሰው ደግሞ ሽማግሌዎቹን መጠየቅ ይሻላል እንላለን።

የመብት ታጋዮቹን ደገፋችሁ በሚል የወሲብ አሉባልታ የተነዛባቸው ጠነከሩ እንጂ ሸብረክ ሲሉ አላየንም። ባልሰሩት የነፍስ ግዳይ የተወነጀሉት አሁንም እስር ቤት ገብተው አላየንም። ከመብት ተከራካሪዎቹ ቃለ አባባል እንውሰድ " እኛ የእምነትና የእውነት ድሃ አይደለንም" የሚል ነው። ፍርድ ቤት ይለየን እንደተባለው እነሆ ፍርድ ቤት እየለየው ነው። ማሸነፍን ግን አላየንም።

ውድ አንባብያን ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት የቦርድ አባላት ከሳሾችን ከዓመት በፊት ከቤተክርስቲያን እናባራችሁ ብለው በወሰኑባቸው ማግስት አታባርሩንም በሚል ስማቸው ተካቶ ከነበረው 28 ተባራሪዎች ውስጥ የሆኑ ምእመናን ክስ መመስረታቸው ይታወሳል። በመሆኑም የነበረውን በየጊዜው የፍርድ ቤት ውሎ መረዋ በወቅቱ የዘገበው ጉዳይ ነበርና ዛሬ ወደ ኋላ ተመልሶ ሁኔታውን በመተንተን ጊዜአችሁን ከመሻማት ይቆጠባል። ነገር ግን የዛሬ ዓመት ክሱን እናቁም በማለት ከሳሾች ከደጋፊዎቻቻው ጋር በመስማማት ክሱን ቢያቆሙም ቦርዱ እስከዛሬዋ የፍርድ ሰዓት ድረስ ለጠበቃ ያወጣንውን 89,000 ብር ይክፈሉን ሳይከፍሉን ክስ አናነሳም ብለው ሲከራረሩ ቆይ ተው ነበር። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ዳኛው የዚህን ክርክር የመጨረሻ ውሳኔ በመስጠት ገንዘብ መጠየቅ አትችሉም ብለው ብይናቸውን ሰጥተዋል። ይልቅስ ይላሉ ዳኛው ይህንን የእምነት ጉዳይ በቤተክርስቲያን ደንብ በውስጥ ለመፍታት ብትሞክሩ መልካም ነው። በማለት ምክራዊ ብይንም ሰጥተዋል። ከሳሾች ለቦርድ አባላት ፩ ብር (አንድ ብር) እንዲከፍሉ እንደተወሰነባቸው ደግሞ የነገሩን የመብት ተከራካሪው ቡድን አባል ለዚህ ምእመናንን እርዳታ አንጠይቅም በማለት እየሳቁ ነበር።

ይህ ቦርዶቹ የሚጠይቁት የጠበቃ ገንዘብ ባለፈው አወጣን የሚሉትን ከ140,00 ብር በላይ የሆነውን አያጠቃልልም። በቅርቡ መረዋ የደረሰውን የቦርድ አባላት ባለፈው ፩ ዓመት ተኩል ለጠበቃ ከፈልን ብለው ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የ 89,000 የወጭ ሰንጠረዥና ከሳሾች በሁለት ዓመት ለጠበቃ ከፈልን የሚሉትን 21,593 ብር የወጭ ሰንጠረዥ ያጠቃለለ በገጹ ላይ እንደሚያትም ቃል ይገባል። ከየትም ይሁን ከየት ማንም ከፈለው ማ ከፋዩ የቤተክርስቲያናችን አባላት ያዋጡት ገንዘብ ነውና። ለአባላት ይጠቅም ዘንድ በእጃችን ያለውን ማናቸውንም መረጃ እንዳስፈላጊነቱ ለማሳወቅም እንደምንጥር ሰንናገር በእርግጠኝነት ነው።

ለመንፈሳዊ አባቶች ያለንን አድናቆትና አክብሮት እየገለጽን የኛን ወገን ዜና ማሰራጫ ሌላ መድረክ ስለሌለን ይህንን የመተንፈሻ ገጽ መጠቀማችንን እንዲረዱልን እንወዳለን።

ውድ ምእመናን ከኛ ወገን የሚተላለፍ መልእክት አለን

ከጎናችን ሆናችሁ ለከረማችሁ፣ ለእውነት ስለቆማችሁ፣ ለተሰደባችሁ፣ ለተባረራችሁ፣ ሁሉ ሚካኤል ዋጋችሁን ይክፈላችሁ እንላለን። እኛና እናንተ እንቅልፍ ተኝተን እናድራለን እንቅልፍ ያጡ ሌሎች ናቸው።
እኛና እናንተ በእሳት ተፈትነን የሕይወት ጓደኛ ሆነናል።
በየወንዙ የሚማማሉት ሌሎች ናቸው።
እኛ ትናንትናም ዛሬም ትክክል ነበርን፣ ለሰላምና ለአንድነት ታግለናል።
አቋማቸውን እንደጥላ የማያምኑት ሌሎች ናቸው።

ሚካኤል ፍርድ እየሰጠ ነው። ለክፋት በቆመው ላይ የዘላለም ፍርድ ይስጥ።

እኛ ማንንም አንጠላም ለሚጠሉን እንጸልያለን።
በማንም ላይ አንፈርድም፣ በሚፈርዱ እናዝናለን።
ማንም ከስራ እንዲወጣ አንፈልግም፣ ይህን ለሚያስቡ ሱባኤ እንገባለን።
በማስፈራራት አንፈራም ከጥል ይልቅ ለፍቅር እንሰግዳለን።
ቤተክርስቲያናችን እንደሚኖር እኛ ግን እንደምናልፍ እናምናለን።
ቤተክርስቲያን የአባቶችና የክርስቲያን ስብስብ እንጂ ሕንጻና ገንዘቡ ነው ብለን ለደቂቃም አናምንም።

ለሰላም እንጸልይ።

እንኳን ደስ አለን።

Monday, January 23, 2012

የጊብሰን የጠበቆች ስብስብ የሕግ ጠበቃ / THE GIBSON LAW GROUP ATTORNEYS AT LAW

 
THE GIBSON LAW GROUP
ATTORNEYS AT LAW 1801 N. HAMPTON RD., STE. 370
DESOTO,TEXAS75115
my.lawyer@sbcglobal.net
Telephone (972) 291-9300 Facsimile (972) 291-0636
January 10, 2012
Via Facsimile (214) 224-7555 Via Facsimile (214) 296-9662
 
Steven C. Metzger
3626 N. Hall St., Ste. 800
Dallas, TX 75243
 
Bruce Thomas
1825 Market Center Blvd., Ste. 200
Dallas, TX 75207
 
Re: Mekonen, et al. v. Retta, et al.
Cause No. 10-05578-E in the 101st District Court
Gentlemen:
This letter is sent pursuant to Texas Rule of Evidence 408 and is intended for settlement purposes only.
I have been informed that your clients defendants Dr. Girma Wolde Rufael and Abera Pitta were recently defeated for re-election to the St. Michael's board of trustees. I have also been informed that the current board desires to resolve this lawsuit amicably, to move past our clients' dispute, and to return St. Michael's to the peaceful sanctuary it once was.
To that end, my clients and the 150 or so current and former members of St. Michael's who support them spiritually and financially are prepared to forgo any further challenges, provided your clients lay down their swords as well. More specifically, the plaintiffs in this case, and all those who support them, are prepared to forego planned federal litigation provided that your clients dismiss their claims, suspend all of the recent amendments to the bylaws, reinstate all disenfranchised members, and appoint a committee representing all of the interests of the church to review and, if necessary, revise the existing bylaws.
I recognize that this is not in the nature of a traditional settlement proposal and may be difficult to document, but you know_ that this is not a traditional case. I also suspect that, regardless of your clients' formal position in this lawsuit, both you as experience counselors and they recognize that this dispute will continue in one fashion or another in one venue or another until the parties truly achieve peace. Please, therefore, understand and encourage your clients to accept that it is peace my clients desire. As such, we trust that this proposal will be received with the same good faith that it is made.
 
Counsel
1110/2012
Page2
Finally, I understand that the board of trustees has a meeting this evening. I would ask that you present this proposal to them immediately, so that they will have adequate time to consider it this evening.

Thank you.
David . Gibson cc: Clients

Wednesday, January 18, 2012

It is Blessing to live this day and able to communicate to you. NO NEWS IS GOOD NEWS!

      ውድ ምዕመናን! የእግዚአብሔር ሰላምታችንን እናቀርባለን።

ምንም ጊዜው ቢራዘም፣ የሰላም ኮሚቴ ሥራውን እየሠራ ነው። የሕዝብንም አደራ እንደጠበቀ ነው።  ይህ በግንቦት 2010፣ ከ200 ያላነሱ ምዕመናን የመረጠው 9 የሰላም ኮሚቴዎች  ሥራችን ወደ ማገባደድ ላይ ናቸው። ሥራቸው ተፈፀመ የሚያሰኘው ሪፖርታቸውን ለታዘዙት አደራ ከፈፀሙ በኋላ እስከሚያቀርቡና ምዕመናኑ እስከሚያሰናብታቸው ድረስ ነው። ይኸንንም ለመፈፀም የሚያስፈልገው፣ ከአንድና ከሁለት ጊዜ በማይበልጥ፣ ከኮሚቴና ከንዑስ ኮሜቴዎች ጋር ስብሰባ ካደረገ በኋላ ታላቅ የሕዝብ ጥሪ እንደሚያደርግ ለምዕመናን ለማሳሰብ እንወዳለን።  ትዕግሥት እንደማር ወለላ ትጣፍጣለች።

የሰላም ኮሚቴ 
የሕዝብ ግኑኝነት ክፍል።